የሚጠየቁ ጥያቄዎች
ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች
መልሱን ከታች ማግኘት ካልቻሉ፣ እባክዎን የእውቂያ ቅጹን ይጠቀሙ ወይም በኢሜል ይላኩልን. lenegewa2016rsd@gmail.com
ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድና የከተማችን ከንቲባ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመረቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
ወደ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ለተለያዩ የተሃድሶና የተለያዩ የክህሎት ስልጠናዎችን ለመሰልጠን፣ በጎዳና ላይ በልመና የሚኖሩትን፣ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩትን፣ ከስደት ተመላሽ የሆኑትንና በየቤታቸው ገቢ የሌላቸውንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙትን ሴቶች ከሁሉም ክፍለ-ከተሞች በማሰባሰብ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል
ለስልጠና የገቡ ሰልጣኞች ከተሃድሶና የተለያዩ የክህሎት ስልጠናዎችን ስልጠና ጎን ለጎን ነጻ የጤና ህክምና፣ የምግብ አገልግሎት የስፖርትና የጂም አገልግሎት የአልባሳትና ሌሎች ነገሮችን በግቢው ውስጥ እንዲሟሉላቸው ይደረጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዱ ሰልጣኝ በግልና በቡደን የምክር አገልግሎት ከማገኘቱም በላይ ከጤናው ጋር በተያያዘ የስነ-አእምሮ ህክምና እንዲያገኙ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል
ስልጠናቸውን ጨርሰው ወደ ስራ ሲሰማሩ የስራ እድል በመፍጠር፤ የማቋቋሚያ በጀት በመለገስና አስፈላጊ የሆኑ የመጠቀሚያ ቁሳቁሶችን በማሟላት ረገድ የግል ባለሃብቱና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባብር ክቡር የሆነውን የሰው ልጅን በተለይም ደግሞ ሴቶችን ከወደቁበት ቦታ በማንሳት ነጋቸውን ብሩህ ተስፋ ከመመኘት በዘለለ እውን እዲሆን ተግቶ የሚሰራ እና ለወደፊትም በትጋት የሚሰራ የሚሰራ ተቋም ነው።
ጥያቄህን ጠይቅ
መልሱን ከታች ማግኘት ካልቻሉ እባክዎን መልእክት ይላኩልን.